Pages

Monday, April 21, 2014

ንገሪኝ ሰበታ፥ አጫውችኝ ቡራዩ

Poem: ንገሪኝ ሰበታ፥ አጫውችኝ ቡራዩ

በቃ መሄዴ ነዉ ምን አባቴ ላድርግ?!
እኔ ጉልበት የለኝ ከወረራ የሚታደግ
የፈለገ ሲያርሰኝ
ወገቶ ስያደማኝ
ከፈጣሪ በቀር
ማን ነዉ አቤት ያለኝ፦
በጦር እየበሱ
ሆድ-ዉሀዬን ሲያፈሱ
በመረዛማ ኬሚካል ወንዞቼን ሲያረክሱ
ብቻዬን ስቃጠል በደገኞች ሞፈር
ማን ነዉ የደረሰልኝ ከሀገሬ ምድር?
እንግድህ ልጆቼ
ዛሬም እንደ ጥንቱ
ለዚህ ሁሉ ጥቃት
ዝም ከሆነ መልሱ
በቃ መሄዴ ነዉ ልሰናበታችሁ
እንገናኝ ይሆናል ፈጣሪ በተዐምሩ
በህይወት ካቆያችሁ።
By Addisu A. Eba: addiuadugna.eba@gmail.com
በቃ መሄድሽ ነው?
ንገሪኝ ሰበታ፥ አጫውችኝ ቡራዩ
እስቲ ምን አመጣው
ምንም ሳታዋይን፥ ጓዝሽን መጠቅለሉን
ልጆችሽ ዬት ገቡ፥ ወደ ምን ላክሻቸው
ደረትሽ ላይ አቅፈሽ፥ ብዙ ያኖርሻቸው
ምን በድለው ኖረዋል፥ ለምን በተንሻቸው
ጉሌሌዎችን ብለሽ ከሆነ፥ መንገድ የጀመርሽው
እሱን አታስቢ ቆዩ ከሸኟቸው
ባታውቂ ኖሯል ሰፉ እንደለላቸው
አላሰብሽበትም፥ ይናፍቅሻል ከርሞ
ዺችስ ፎሌኬ፥ እኔ ብየሻለሁ
ከበሮ ደላቂ፥ ልብ የሚያስከዳ
ዶሮሽ ገና ሳይጮህ፥ ጩሄት የሚያሰማ
ይወሪሻል ተይ፤ ተይ ግን ሱሉልታ
ከብቶችሽን አባሮ፥ ድንጋይ ምጭንብሽ
ከላይ ተከናንቦ፥ አር የሚያራብሽ
መጥቶብሻል ይሄው፥ ይቆጭሻል የምር
ገላን እና ሰላሌስ፥ እንዴ ምን ወሰኑ
አገሪ እና ታዴ፥ ሃሳብ ሳይሰጡ
እንዴት፥ እንዴት ሆኖ ዳሌዋ ተዘርግቶ ደጀንን ከነካው
የአድሳባ ጮሌ እትብት እንደገቡ።
By Jireenyaa Dh Yaadataa: jiregnaaa2013@gmail.com

No comments:

Post a Comment