በምስራቅ አፍሪካ አቻ ያልተገኝላት ብቸኛዋ አምባገነን በንፁሀን ሕዝብ ላይ አፈና፣ እንግልት፣ ግድያ ፣ እስር ፣ ዛቻ እናማስፈራራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየገዘፈ እና እየተበራከተ የመጣበት ወይም የተስፋፋበት አምባገነኖች እንደፈለጉ ያሻቸውንየሚፈፅሙባት ሀገር ኢትዮጵያ ናት። ሲፈልጉ ወገኖቻችንን በተናጠል ያፍናሉ፣ ያስራሉ፣ይገድላሉ። በሌላም ጊዜም በጅምላይጨፈጭፋሉ። ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ስልጣኑን በበላይነት ይዘው እና ተቆጣጥረው የፈለጉትን እና ያሻቸውን ያደርጋሉ።የሀገራችንን ሀብት ከመሟጠጣቸውም በላይ የተወስኑትን የስርዕቱ አቀንቃኞች ለመጥቀም በሚሊዮን የሚቆጠረውን ጭቁኑንየኦሮሞ አርሶ አደር ሕዝብ ከቀዬው ለማፈናቀል እና ማንነቱን ለማጥፋት ማቀድ እና ማሴር ከግብ ይደርሳል ብሎ ማሰብ ዘበትነው።
ሕዝብን ይዘልፋሉ፣ያስራሉ፣ይገርፋሉ፣ይገድላሉ - አምባገነኖች።
በአንድ ወቅት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ስርዓቱ በፈጠረው ምክንያት ስራ አጥ ወጣቱን ¨¨አደገኛ ቦዘኔ¨¨ በማለትበመሳደባቸው ውጤቱ ምን እንደነበረ በ97ቱ የምርጫ ወቅት በሚገባ አምባገነኖቹ አይተውታል። ዛሬ ደግሞ የአምባገነኖቹቁንጮ የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሜቴ አባል እና የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ አቶ አባይ ፀሐዬ ¨¨ ልክ እናስገባቸዋለን!¨¨የሚለው ዛቻ ምን ሊያስከትል እንደሚችል ሳይገነዘቡት ቀርተው አይመስለኝም። አቶ አባይ ፀሐዬ ከ40 ሚሊያን በላይየሚገመተውን የኦሮሞ ሕዝበ ከፊንፊኔ ማስተር ፕላን ጋር ተያየዞ የተናገሩት ንቀት ያዘለ ዛቻቸው የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽአምባገነኖች እንደሆኑ ሳይውል ሳያድር የሚያዩት ጉዳይ ይሆናል። በኦሮሞ ሕዝብ ማንነት እና ህልውና ጉዳይ ላይ ለተሰነዘረውእና ለተቃጣው ዛቻ እና ማስፈራሪያ ምላሹ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ዛሬ በአምባገነኖች ዛቻ እናማስፈራራት የሚበረከክ ትውልድ ሳይሆን ጨቋኞቻችንን የሚያንቀጠቅጥና ለሕዝብ ትልቅ ለውጥ የሚያመጡ ታላላቅ ጀግኞችብዙ ¨¨ ሞት አይፈሬ¨¨ ወጣት ትውልድ የተፈጠረበት ዘመን ነው።
በተለያየ ጊዜም ይህ የታየበት ሁኔታ አለ። የፊንፊኔን ማስተር ፕላን ጨምሮ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመቃወም ወጣቱቁርጠኝነቱን እና ጀግንነቱን አሳይቷል። ምንም እንኳን አምባገነኖች በግፍ ላይ ግፍ በወንጀል ላይ ወንጀል መደራረብ የለመዱቢሆንም የተጨቆነው ሕዝብ የግፍ አገዛዝ አይበቃም ወይ እያለ ያለበት ዘመን ነው። በማንነት እና በህልውና ላይ ለተቃጣውዛቻ እና ማስፈራሪያ ለአምባገነኖቹ ማፈሪያ እና ውድቀት እንጂ ለተበደለ፣ ለተከፋ፣ ለተጨቆነ፣ ለታፈነ እና ለተበዘበዘ ደግሞየበለጠ ለነፃነቱ ትግል የሚያነሳሳ ነው። ትውልዱ ያደረገው እና እያደረገው ያለው ተጋድሎ እና ፣ የከፈለው እና እየከፈለያለውን መስዋትነት ለመገመት አስቸጋሪ አይደለም። አሁንም የተቃጣብንን የማንነት ማጥፋት ዘመቻ ለመመከት ከምንጊዜምበጠነከረ መልኩ በተመሳሳይ የአምባገነኖቹ ግፍ እየደረሰበት ካሉ ሌሎች ሕዝቦች ጋር በጋራ በመሆን ለትግሉ ቁርጠኝነትያሳየበት ወቅት ነው።
በዚያች ሀገር ለመኖር የግድ የገዝው ፓርቲ አባል ወይም ደጋፊ መሆን ያስፈልጋል፤ ያልሆነ ግን በጥርጣሬ ይታያል። የአገር ሀብትአትመንዝሩ፣ መልካም አስተዳደር ይምጣ፣ የዲሞክራሲ እና የሰብዓዊ መብቶች ይከበሩ፣ ለህግ ተገዢ ሁኑ ብሎ የገዥውን ፓርቲበግልፅ የሚናገር ወይም የሚመክር ግለሰብም ሆነ ድርጅት ደግሞ ፀረ ሰላም፣ ፀረ ልማት፣ፀረ ሕዝብ፣ ፀረ ዲሞክራሲ የሚልታፔላ ይለጥፉለታል። በዚህም አያበቁም አፍነው ይገድላሉ ወይም በሐሰት ክስ ወደ ከርቸሌ ወይም ወደ ዘብጥያ ያወርዳሉ።
በዚያች ሀገር ሰላም እና ነፃነትን ለማምጣት እና ለመኖር የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ከተጨቆኑ እና በተመሳሳይ ያአምባገንኖች የግፍ አገዛዝ ያንገሸገሻቸው ብሔር ፣ ብሔረሰብ እና ሕዝብ ከጎኑ አሰልፎ እና ተባብሮ አንድ ወጥ ትግል ታግሎ በመጀመሪያጨቆኙን እና አምባገነኑን ወያኔ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ነው። አምባገነኑ የወያኔ መንግስት ከተወገደ በኋላለሁሉም የምትስማማ ሰብዓዊ፣ዲሞክራሲያዊ እና የሕግ የበላይነት የሚከበርበት ምቹ ሀገር መፍጠር ያስፈልጋል። ይህ የምሆነውልክ እንደ ኦሮሞ ሕዝብ የግፍ አገዛዝ ያንገሸገሻቸው ብሔር፣ ብሔረሰብ እና ሕዝቦች ከኦሮሞ ሕዝብ ጎን በመቆም መታገልሲችሉ ብቻ ነው።
No comments:
Post a Comment